Lyrks
Lyrks
Lyrks
Cover Art

አፄ ቴዎድሮስ (Atse Tewodros) Lyrics by ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro)

2017

የሰገደላት ውበቱ
፤ ያቺን የቃል መስታይት
ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ
፤ ቆሞ ስቃዩዋን ላለማየት
የወደቀላት ውበቱ
፤ ያቺን የቃል መስታይት
ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ
፤ ቆሞ ስቃዩዋን ላለማየት
ኸ ... ናና ሲል ናና ...
ደርሶ ባያስጥለው ፤ ገብርዬ ከስለት
ጀግናው ተፈተነ ፤ በመቅደላ አቀበት
ተዋከበና ፤ ተዋከበና
ወዲህ ዞር ቢል ፤ ሰው የለምና
ገብርዬ ሲወድቅ ፤ ቀኙ ዛለና
አረሩን ስቦ ፤ ጠጣው ያ ጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
ኸ ... ናና ሲል ናና ...
ደርሶ ባያስጥለው ፤ ገብርዬ ከስለት
ጀግናው ተፈተነ ፤ በመቅደላ አቀበት
ተዋከበና ፤ ተዋከበና
ወዲህ ዞር ፤ ቢል ሰው የለምና
የነደደ እሳት ፤ ክንዱን ተ'ርሶ
ጨክኖ ካሣ ፤ ጋተና ኮሶ
ሞተ 'ላንድ አገር ፤ ባንዲራ ለብሶ
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
ካሳ በል አግሳ ፤ እንደ አንበሳ
የቋራ አንበሳው ዳግማሮስ ካሳ ፤ በል አግሳ
ካሳ በል አግሳ ፤ እንደ አንበሳ
ያንዲት እናት ሀገር ክብርዋ ከቶም ሳይረሳ
ካሳ በል አግሳ ፤ እንደ አንበሳ
ንቃ በመንፈስ ላንድነት ፤ ካሳ ተነሳ
ካሳ በል አግሳ ፤ እንደ አንበሳ
አንተ የሞትክላት ሀገር ፤ ክብርዋ ሳይረሳ
ካሳ በል አግሳ ፤ እንደ አንበሳ
ንቃ በመንፈስ ላንድነት ፤ ካሣ ተነሳ
አንተ የሞትክላት አገር ፤ ክብሯ ሳይረሳ
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
ኦ ...
ጎንደር ጎንደር ፤ የቴዎድሮስ አገር
ያንዲት ኢትዮጵያ ፤ ዋልታና ማገር
ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ፤ ቴዎድሮስ ወድቆ
ኧረረ ኧረረረ
ኧረረ ኧረረረ
አምጡ ቆርጣችሁ ፤ ከሹሩባው ላይ
ኪዳን እንሰር ፤ እንዳንለያይ
ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ፤ ቴዎድሮስ ወድቆ
አረጀች እያሉ ፤ ሰዎቹ ሲያሙሽ
አረጀች እያሉ ፤ ሰዎቹ ሲያሙሽ
ሙሽራ ነሽ ጎንደር ፤ ይሰፋል ልብስሽ
ተይ ድማም ፤ ተይ ድማም
ተይ ድማም ፤ ተይ ድማም
ሳይገላገለው ፤ ህልሙን በሆድ ይዞ
ሳይገላገለው ፤ ሽሉን በሆድ ይዞ
የሚረዳው አጥቶ ፤ ብቻውን ተክዞ
ተክዞ ተክዞ ፤ ስንቱን በሆድ ይዞ
የወገቡን እሳት ፤ ካፎቱ ላይ መዝዞ
የወገቡን እሳት ፤ ካፎቱ ላይ መዝዞ
ጠጥቶላት ሞተ ፤ ክንዱን ተንተርሶ
አያሳዝንም ወይ
ካሣ ካሣ ፤ የቋራው አንበሣ
ዳኘን ዳኘን ፤ አንድ ህልም አሳየን
ዝግባ ሚያሳክለን ፤ አንድ ፍቅር አጥተን
ዝግባ ሚያሳክለን ፤ አንድነትን አጥተን
ከፊት የነበርነው ፤ ከሰው ኋላ ቀርተን
አናሳዝንም ወይ
ጎንደርና ጎጃም ፤ ወሎና ትግራይ
ኦሮሞና ተጉለት ፤ ሆነን አንድ ላይ
ጉራጌና ሃረር ፤ ዶርዜ ወላይታ
ቤኒሻንጉል ሶማሌ ፤ አፋር አሳይታ
ግመሌን ላጠጣት ፤ እንደ አፋር ተጉዤ
ግመሌን ላጠጣት ፤ ቀይ ባህር ተጉዤ
አንድ ገመድ አጣሁ ፤ ልመልሳት ይዤ
'ያንዲት እናት ልጆች ፤ መሆናችን አውቀን
ጎሳና ኃይማኖት ፤ ሳይነጣጥለን
ምን ይሳነን ነበር ፤ ብንተባበር
አናሳዝንም ወይ
ጎንደር ጎንደር ፤ የቴዎድሮስ አገር
ያንዲት ኢትዮጵያ ፤ ዋልታና ማገር
ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ፤ ቴዎድሮስ ወድቆ

About “አፄ ቴዎድሮስ (Atse Tewodros)” by ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro)

Read the complete lyrics to "አፄ ቴዎድሮስ (Atse Tewodros)" by ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro) in 2017. On Lyrks you can follow along with the full text, explore the artist's discography, and discover related songs. The track is often categorized under Pop.

"አፄ ቴዎድሮስ (Atse Tewodros)" is performed by ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro). in 2017 This page provides the full lyric text for fans who want to sing along, study the songwriting, or compare versions across releases. Lyrks organizes lyrics by artist and song slug so you can bookmark and share a stable URL. Music lyrics help listeners connect with emotion, narrative, and rhythm in a track. Whether you are learning English, researching a favorite chorus, or preparing for karaoke, having accurate line breaks and section labels (verse, chorus, bridge) makes the experience easier. We link to the official artist profile on Lyrks where available, including biography snippets, top songs, and chart placements when we have that data. If you enjoy "አፄ ቴዎድሮስ (Atse Tewodros)", explore more songs by ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro) using the links below. Chart and trending pages on Lyrks highlight what listeners are searching for this week. For copyright or correction requests, see our DMCA and contact pages.

View all songs and biography for ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro) · Trending lyrics · Billboard Hot 100

Frequently asked questions

"አፄ ቴዎድሮስ (Atse Tewodros)" is credited to ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro). Songwriting credits may include additional writers listed on the release; check the credits section on this page for linked collaborators.

Album information for "አፄ ቴዎድሮስ (Atse Tewodros)" is not available in our database yet. You can still read the full lyrics on this page.

Visit the ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro) artist page at /artist/teddy-afro for biography, popular tracks, and links to more lyric pages.